የድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ፍቃድ ተከለከለ።

ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ መስቀል አደባባይ ላይ ሊያደርግ ያሰበው ኮንሰርት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍቃድ ሳያገኝ ቀረ። ኢትዮፒካሊንክ ከከተማ አስተዳደር ምንጮቼ አገኘውት ባለው መረጃ መሰረት መስቀል አደብስባይ ለፅጥታ ምቹ ባለመሆኑ ኮንሰርቱ ፍቃድ ሊሰጠው አለመችስሉን ተናግረዋል። ነገር ግን የኮንሰርቱ አዘጋጆች በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርቱን ለማካየድ ድጋሚ የፍቃድ ጥያቄ ማቅረባቸውን እና በሚቀጥለው ሳምንት ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ቴዲ አፍሮ ለአድናቂዎቹ እስከ ዛሬ አብረውት ሰለነበሩ ምስጋና አክብሮት ለማቅረብ በመስቀል አደባባይ የነፃ ኮንሰርት ሊያዘጋጅ እንደሆነ ስራ አስኪያጁ ጌታቸው ማጉዳይ በአንድ ወቅት ለታዲያስ አዲስ በሰጠው ቃለ መጠየቅ መናገሩ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *